Back to Careers
የሥራ መደብ መጠሪያ (Job Title):
የቴክኖሎጂ እና ሶፍትዌር ሽያጭ ተወካይ (Junior Software Sales Representative)
የሥራው ዝርዝር መግለጫ (Job Description):
ስለ ድርጅቱ፦ ድርጅታችን በቴክኖሎጂ እና ሶፍትዌር ልማት ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን፣ የደንበኞቻችንን የሥራ እንቅስቃሴ የሚያቀሉ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን ያቀርባል።
የሥራው አጠቃላይ ዓላማ፦ በቀጥታ በመስክ ላይ በመገኘት (On-the-ground) አዳዲስ ደንበኞችን መፈለግ፣ የድርጅታችንን የሶፍትዌር ምርቶችና አገልግሎቶች ማስተዋወቅ እና ምርቶችን በአካል በመገናኘት መሸጥ።
የሥራው ሁኔታ፦
ጊዚያዊ (ኮንትራት)
ዋና ዋና ተግባራት እና ኃላፊነቶች፦
- አዳዲስ ደንበኞች ሊሆኑ የሚችሉ ተቋማትን እና ግለሰቦችን በአካል በመጎብኘት የሶፍትዌር መፍትሔዎቻችንን ማስተዋወቅ።
- ከደንበኞች ጋር በመገናኘት ፍላጎታቸውን መረዳት እና የድርጅቱ የቴክኖሎጂና ሶፍትዌር መፍትሔ ማቅረብ።
- ስለ ድርጅቱ የሶፍትዌር ምርቶች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ እና ገለጻ (Presentation) መስጠት።
- የሽያጭ ግቦችን ለማሳካት ዕለታዊ እና ሳምንታዊ የመስክ ጉብኝቶችን ማድረግ እና አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት።
- ከደንበኞች ጋር መልካም እና ዘላቂ የሥራ ግንኙነት መፍጠር እና መጠበቅ።
- የመስክ ውሎዎችን እና የሽያጭ እንቅስቃሴዎችን የሚያሳይ መደበኛ ሪፖርት ማቅረብ።
ተፈላጊ መስፈርቶች፦
- በማርኬቲንግ ማኔጅመንት (Marketing Management) ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ላት።
- ድርጅቱን ወክሎ በአካል ለመንቀሳቀስ እና ደንበኞችን ለመቅረብ ሙሉ ፈቃደኝነት ያለው/ላት።
- በጣም ጥሩ የሆነ የመግባባት፣ የመደራደር እና የማሳመን ችሎታ።
- ስለ ቴክኖሎጂ እና ሶፍትዌር መፍትሔዎች ፈጣን የመማር ፍላጎት እና እውቀት ያለው/ላት።
- በራስ የመተማመን መንፈስ እና የሽያጭ ፍላጎት ያለው/ላት።
የሥራ ልምድ፦
0 ዓመት (አዲስ ተመረቂ/ቂዎች ይበረታታሉ)።
ደሞዝ
በስምምነት (ቤዝ + ኮሚሽን)